Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 04, 2026 .

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

 

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
አሁን ባለው ተለዋዋጭና ከቴክኖሎጂ ጋር የተሰናሰለ የንግድ ስርዓት ጋር ሊራመድ የሚችል የንግድ ማኅበረሰብ ለመገንባት አቅምን በስልጠና ማዳበር ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡
ከፍተኛ የማሰልጠን ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተሰጠው ስልጠና በስልጠና ዝግጅት (Training Facilitation) ፣ በሰልጣኝ ማኔጅመንት፣ በስልጠና ዘዴዎች (Training Methodology) ፣ በሰነድ አዘገጃጀት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር፡፡
ለሶስት ተከታታይ ቀናት በጌትፋም ሆቴል ሲሰጥ የሰነበተው ስልጠና አሰልጣኞች ስልጠናዎችን ከመስጠታቸው በፊት አቅማቸው የተገነባ እንዲሆን፣ በተለያዩ ሁኔታዎች እንዲሁም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እንደየ አካባቢው ጸጋ ለውጥ አምጭ ስልጠናዎችን ለመስጠት የሚያግዝ ነዉ ፡፡

  
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ጫፍ ላይ በደረሰችበት፣ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ባደረገችበት እንዲሁም በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር እየተስፋፋ በመጣት በዚህ ወቅት ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን የሚቻለው አቅሙ የተገነባ አመራርና ሰራተኛ ሲኖር ነው፡፡
ሰልጣኞቹም በቀጣይ ለሚሰጧቸው ስልጠናዎች ራሳቸውን ዝግጁ ለማድረግና ውጤት ማምጣት እንዲችሉ ስልጠናዉ ተጨማሪ  አቅም እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከሚሰራቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ የንግዱን ማኅበረሰብ አቅም መገንባት እና ስልጠና መስጠት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia