Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

May 28, 2026 .

በ7ኛው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ የግሉ ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡

በ7ኛው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ የግሉ ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡

ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ የፖለቲካ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የግሉ ዘርፍ ወሳኝ ሚና ይጫዎታል፡፡

ለዚህ ደግሞ የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ ማድረግና ለሀገራዊ መሻሻልና እድገት አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል፡፡

የግሉ ዘርፍ የላቀ ተሳትፎ ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው በምርጫ መሳተፍና ይሆነኛል የሚለውን አካል የሚመርጥበት እድል ነው፡፡ በዚህ ሂደትም በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ እስካሁን ንቁ ተሳታፊ በመሆን ከፍተኛ ሚና ሲጫዎት ቆይቷል፡፡

የፊታችን ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለ7ኛ ጊዜ የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ተዓማኒ፣ ፍትሃዊ፣ አሳታፊና ተቀባይነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የግሉ ዘርፍ ንቁ ተሳታፊ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

በመሆኑም በየደረጃው ያሉ አባል ምክር ቤቶች የንግዱ ማህበረሰብ በዚህ ሀገራዊ ኃላፊነት የበኩሉን እንዲወጣ የማስገንዘብና ተሳታፊነትን የማረጋገጥ ሚናቸውን እንዲወጡ ምክር ቤታችን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የንግዱ ማኅበረሰብ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለሚያደርገው ሁለንተናዊ ተሳትፎ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግሉን ዘርፍ በመወከል ከወዲሁ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

ግንቦት/2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia