Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jan 12, 2026 .

ኢትዮጵያ እና ጃፓን በንግድ እና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ተወያዩ

ኢትዮጵያ እና ጃፓን በንግድ እና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ተወያዩ

▶️ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኩኒሚትሱ አያኖ ከተመራ የንግድ እና ኢንቨስትመንት የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

▶️ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ከ35 በላይ የጃፓን ኩባንያዎች ለተውጣጡ 48 የቢዝነስ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ስላለው አዲስ እና ምቹ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ገለጻ አድርገዋል። ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት  አማራጮች እንዲሳተፉም  ጥሪ አቅርበዋል።


▶️ ሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው የገለጽት ሚኒስትሩ፤ በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን የግንኙነት መድረኮችም ጠንካራ ትብብር እንዳላቸው  አንስተዋል።
ጃፓን ለኢትዮጵያ  ለምታደርጋቸው የልማት ድጋፎች ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

▶️ በንግድ እና ኢንቨስትመንት እየተሻሻለ የመጣው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የበለጠ መጠናከር እንዳለበትም  ተናግረዋል፡፡

▶️ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኩኒሚትሱ አያኖ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ እና ጃፓን ግንኙነት በንግድ እና ኢንቨስትመንት የበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አንስተዋል።

▶️ ሚኒስትር ዴኤታዋ ለልዑካን ቡድናቸው ለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው፤ ነገ በሚካሄደው የኢትዮ-ጃፓን ቢዝነስ ፎረም እንደሚሳተፉ ጠቁመወል።

▶️ ፎረሙ የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ረገድ ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረውም ተገልጿል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia