Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 30, 2026 .

ኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው የማዕድን ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሄደ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው የማዕድን ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ውይይት የተለያዩ ተቋማት እና በማእድን ዘርፍ የተሠማሩ ኩባንያዎች ተወካዮች በተገኙበት ተካሄደ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በመንግስት ከተለዩ ዘርፎች አንዱ ማዕድን ሲሆን ዘርፉን የበለጠ ለማሳደግ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረኮች እየተዘጋጁ ሥለመሆናቸው አንስተዋል።

የማዕድን ዘርፉ ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ለኢንዱስትሪ ልማትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ያለውን ድርሻ ለማሳደግ በመንግሥት፣ በግሉ ዘርፍና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል የተጠናከረ ቅንጅት እንደሚያስፈልግም በውይይቱ ተመላክቷል።

ማእድን ከቁፋሮ እሥከ ወጭ ንግድ እና እሴት መጨመር ሰንሰለት ባለው ሂደት ያሉበትን የሎጂስቲክ ፣ የጸጥታ፣ የጂኦሎጂካል መረጃ፣ የትራንስፖርት፣ የፖሊሲ እና አሠራር እንዲሁም የተቋማትን ቅንጅታዊ ችግሮች መፍታት እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተንጸባርቋል።

የዉይይት መድረከ ከማዕድን ሚኒስቴርና ከሳይፕ ኢትዮጵያ (CIPE Ethiopia) ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል የተዘጋጀ ነው።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia