ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በአፍሪካ ኅብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው በአፍሪካ ኅብረት በመሾምዎ እንኳን ደስ ያልዎ!


ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በአፍሪካ ኅብረት የሰው ሠራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው በአፍሪካ ኅብረት በመሾምዎ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እና በራሴ ስም እንኳን ደስ አልዎት ለማለት እወዳለሁ።
በእርስዎ አመራር ባለፉት ጥቂት ዓመታት ፣ ኢትዮጵያ በዲጂታላይዜሽን እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፎች ያስመዘገበችው እድገት ከፍተኛ አፈጻጸም ያሳየ ነው።
የዲጂታል መሰረተ ልማትን ማስፋፋት፣ የኢ-መንግሥት (e-government) አገልግሎቶችን ሥራ ላይ ማዋል፣ በፈጠራ ሥነ-ምህዳር ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩትን መቋቋሙ እንዲሁም ሀገራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስትራቴጂ መንደፋ ለግሉ ዘርፍ እድገትና ለውጥ ጠንካራ መሰረት የጣሉ ተግባራት ናቸው።
በመንግስት እየተከናወኑ ያሉ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ለግሉ ዘርፍ እያስገኙት ካለው ጠቀሜታ ባሻገር የዲጂታል መሰረተ ልማትን መስፋፋትና የኢ-መንግሥት (e-government) አገልግሎቶችን ሥራ ላይ ማዋል የንግዱ ማኅበረሰብ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኝ፣ የንግድ አሰራሮች ብሎም የወጪ/ገቢ ንግድ እንዲቀላጠፉ፣የፋይናስ ዘርፉ እንዲዘምን ወዘተ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ከመሆኑ አንፃር ምስጋናችንን እናቀርባለን።
እንኳን ደስ ያልዎ!
ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት






I would like to extend my heartfelt congratulations to H.E. Dr. Abiy Ahmed on your appointment as the African Union Champion for Artificial Intelligence and Digital Health.
On behalf of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations and myself, I am pleased to convey this message of appreciation.
Under your leadership over the past few years, Ethiopia has made notable progress in the areas of digitalization and artificial intelligence. Key initiatives, including the expansion of digital infrastructure, the implementation of e-government services, investment in the innovation ecosystem, the establishment of the Artificial Intelligence Institute, and the development of a national AI strategy, have laid a strong foundation for private sector growth and transformation.
Moreover, alongside the ongoing comprehensive economic reforms, these efforts have brought tangible benefits to the private sector. The expansion of digital infrastructure and the rollout of e-government services have improved access to efficient public services for the business community, streamlined trade processes such as import and export, and supported the modernization of the financial sector.
In this regard, we once again express our sincere appreciation.
Congratulations.

