ውጤት ያስመዘገቡ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤቶችና ባለድርሻ አካላት ሽልማት ተበረከተላቸው።




ውጤት ያስመዘገቡ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤቶችና ባለድርሻ አካላት ሽልማት ተበረከተላቸው።
በ13ኛው የኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም ላይ ውጤት ላሥመዘገቡ ምክር ቤቶች እንዲሁም ለልምድ ልውውጡ ፕሮግራም የላቀ ተሣትፎ ለነበራቸው ባለድርሻ አካላት ነው ሽልማቱ የተበረከተው።
ሽልማት የተበረከተላቸው ለአባላትና ለንግዱ ማኀበረሠብ በሚሠጧቸው አገልግሎቶች የላቀ አፈጻጸም ላሥመዘገቡ ምክር ቤቶች፣ የክልል የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤቶች፣ የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤቶች፣ ማኀበራት፣ ለ13ኛው የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም በአጋርነት ለሠሩ ባለድርሻ አካላት ነው።
ሽልማቱን ያበረከቱ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና የኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር፣ የሸገር ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት መጋቢ ሥርዓት ቀሲስ ታየ ለታ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዓይናለም አባይነህ ናቸው።



የተበረከተውም የዋንጫ፣ ጋቢን ጨምሮ ባህላዊ መገልገያ እንዲሁም የሠርተፊኬት ሽልማት ሲሆን የኢራን ኤምባሲም ከሸገር ከተማ ጋር በሚያደርጋቸው የትብብር ሥራዎች ተሸላሚ ሆኗል።
የሸገር ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ የጅማ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት እንዲሁም የነቀምቴ ከተማ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ባስመዘገቡት ውጤት የልዩ ዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል።
14ኛው የኦሮሚያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም በጅማ ከተማ እንደሚዘጋጅም በዝግጅቱ ላይ ተገልጿል።

