Oct 12, 2025 .
የሀገራችን ሐይቆች የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የተለያዩ ዓይነት ጀልባዎችን ለአንድ ዓመት ያህል ከማናቸውም ቀረጥ እና ታክስ ነጻ ሆነው ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ………

የሀገራችን ሐይቆች የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ሲባል የገንዘብ ሚኒስቴር በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 (እንደተሻሻለ) አንቀጽ 129 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በንግድ ሥራ ላይ የተሠማሩ ሰዎች በሞተር ኃይል የሚሠሩ የተለያዩ ዓይነት ጀልባዎችን ለአንድ ዓመት ያህል ከማናቸውም ቀረጥ እና ታክስ ነጻ ሆነው ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያስገቡ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱ ይታወሳል።
ይህን አስመልክቶም የገንዘብ ሚኒስቴር በቀን 06/01/2018 ለአስፈፃሚው አካል ማለትም ለጉምሩክ ኮሚሽን ያሳወቀበትን ደብዳቤ ከላይ አያይዘናል።

