የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታወን ONE THIBAULT HOTEL ፤ በምክር ቤቱ የ2019 በጀት ዘመን ረቂቅ ዓመታዊ እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን በማከል አፅድቆታል።


የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታወን ONE THIBAULT HOTEL ፤ በምክር ቤቱ የ2019 በጀት ዘመን ረቂቅ ዓመታዊ እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን በማከል አፅድቆታል።
በምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ሰብሳቢነት በተካሄደው የ2019 በጀት ዘመን ረቂቅ ዓመታዊ እቅድ ውይይት፤
ቦርዱ ከፅ/ ቤቱ የቀረበለትን የስራ እንዲሁም የበጀት እቅዶች በዝርዝር የተመለከተ ሲሆን፤ ምክር ቤቱ የሚጠበቅበትን የግል ዘርፍ ተልዕኮ ከማሳካት አንፃር የቀረበው ዕቅድ ሙያዊ መሆኑን በማንሳት በተጨማሪም ሊከናወኑ የሚገባቸው ወቅታዊ ቁልፍ ተግባራትን በማከል በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

የቀረበው ዕቅድ የምክር ቤቱን የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ፣ ወቅታዊ የግሉ ዘርፍ ነባራዊ ሁኔታን፣ በአገራችን ያለውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ፣ የግሉ ዘርፍ ፍላጎቶችን፣ የምክር ቤቱን ቀጣይ የለውጥ ጉዞን ብሎም ያለውን አቅም መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ያነሱት የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ለዕቅዱ መሳካት የምክር ቤቱ የዴሬክተሮች ቦርድ፣ የፅ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች ለአፈፃፀሙ ተግተው እንዲንቀሳቀሱ እንዲሁም ተባባሪና የባለድርሻ አካላት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራ የቦርድ አባላትን፣ የምክር ቤቱን ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች የባለድርሻ አካላትን ያካተተ ልዑክ በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታወን የስራ ጉብኝት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

