የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ከናይጄሪያ የንግድ ኢንዱስትሪ ማዕድንና ግብርና ማህበራት ም/ቤት ጋር በአቡጃ ተወያይቷል።

የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት በኢትዮጵያና በናይጄሪያ መካከል ያለዉን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከአቻዉ የናይጄሪያ የንግድ ኢንዱስትሪ ማዕድንና ግብርና ማህበራት ም/ቤት ጋር በናይጄሪያ አቡጃ ተወያይቷል።
የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ም/ል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዓይናለም አባይነህ እና ዋና ፀሐፊዉ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በናይጄሪያ አቡጃ በመገኘት ከናይጄሪያ የንግድ ኢንዱስትሪ ማዕድንና ግብርና ማህበራት ም/ቤት ጋር ባደረጉት ዉይይት የኢ/ን/ዘ/ማ/ም/ቤት ም/ል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዓይናለም አባይነህ የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት በማንሳት አሁን በኢትዮጵያ በተፈጠረዉ ምቹ ሁኔታና ከተካሄዱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ማሻሻያ አኳያ የሁለቱ አገራት ግንኙነት በተለይም በንግድና ኢንቨስትመንት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አብራርተዋል።

የኢ/የን/ዘ/ማ/ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ የም/ቤቱን ታሪካዊ ዳራና አሁን ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ያቀረቡ ሲሆን በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተግባራዊ ባደረጋቸዉ ሪፎርሞች አሰራሩን በማዘመን በመንግስትና በግሉ ዘርፍ መካከል አገናኝ ድልድይ ሆኖ ከመስራት ባሻገር በአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ዉስጥ የግሉ ዘርፍ ሚና ጉልህ ድርሻ ኢንዲኖረዉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ከመንግስት ጋር ተቀራርቦ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በሌላ መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት ከወሰዳቸዉ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ማሻሻያ አንፃር አሁን ያሉትን የኢንቨስትመንት አማራጮችንና አገሪቷ ያላትን ምቹ ሁኔታዎችን በዝርዝር በማቅረብ የናይጄሪያ ባለሀብቶችም በዚህ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በሁለቱ አገራት መካከል ያለዉን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እንዳያስፋፉና እንዲያጠናክሩ ጥሪያቸዉን አቅርበዋል ዶ/ር ቀነኒሳ።



