Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 17, 2026 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቢዝነስ አመራር አካዳሚ ከካይዘን የልህቀት ማዕከል እና ከጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (JICA) ጋር በመተባበር ለምክር ቤቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ለአባል ምክር ቤቶች አመራሮች ስልጠና እየሰጠ ነዉ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቢዝነስ አመራር አካዳሚ ከካይዘን የልህቀት ማዕከል እና ከጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (JICA) ጋር በመተባበር ለምክር ቤቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ለአባል ምክር ቤቶች አመራሮች በቢሾፍቱ ከተማ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነዉ።

ስልጠናው በካይዘን ፅንሰ-ሀሳብ፣ በምርታማነት ማሻሻል እና በቢዝነስ አመራር ላይ ያተኮረ ነው።

ስልጠናዉን በንግግር የከፈቱት የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፊራ የአመራር አቅምን መገንባት ለተቋማት ውጤታማነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ ስልጠናው አላስፈላጊ የሀብት ብክነትን በማስቀረት ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ይህ የሁለትዮሽና የሶስትዮሽ ትብብር ስልጠና የተዘጋጀዉም የአመራሩን የአሰራር ብቃት በማጎልበት የምክር ቤቱን አገልግሎትና አጠቃላይ ምርታማነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ገልፀዋል።

የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸዉ፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናው ለተቋሙ ተልዕኮ ስኬት ያለውን አስፈላጊነት ከምክር ቤቱ ግቦችና አቅጣጫዎች ጋር በማያያዝ አብራርተዋል።

❇️❇️❇️

The Business Leadership Academy of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), in collaboration with the Kaizen Center of Excellence and the Japan International Cooperation Agency (JICA), is conducting a capacity-building training in Bishoftu for its Board of Directors and leaders of member chambers.

The training focuses on the Kaizen philosophy, productivity enhancement, and business leadership. ECCSA President, Mr. Sebsib Abafira, with his opening remaqk, emphasized that building leadership capacity is vital for institutional effectiveness, adding that implementing such practices will enhance productivity by preventing unnecessary resource wastage.

This joint collaborative training is organized to strengthen leadership skills and elevate the overall service delivery and productivity of the Chamber, Mr. Rebsib added. Dr. Kenenisa Lemi, Secretary General of ECCSA, on his part highlighted the importance of capacity building in aligning with the Chamber’s overarching mission and strategic goals.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia