የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከቻይና የዥጂያንግ የንግድና ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን ልዑካን ጋር ተወያየ።



የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከቻይና የዥጂያንግ የንግድና ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን ልዑካን በኢትዮጵያ ባሉ የንግድና ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎችና ምክር ቤቱ እየሠራቸው ባሉ ሀገራዊ ሚናዎች ዙሪያ ተወያየ።
ከልዑካን ቡድኑ ጋር የተወያዩት የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ሔለን ረታ ሲሆኑ የዥጂያንግ ንግድና ኢንዱስትሪ ፌደሬሽን ምክትል ሊቀመንበር ሊ ሊፈይ ተሳታፊ ሆነዋል።
ከፌደሬሽኑ እና ከተለያዩ ኩባንያዎች የተውጣጡት የልዑኩ አባላት በሪል እስቴት ግንባታ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኃይል አቅርቦት እና በሌሎችም ዘርፎች በኢትዮጵያ የመሥራት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል።


The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) held discussions with a delegation from the Zhejiang Federation of Industry and Commerce of China on Ethiopia’s trade and investment opportunities and the Chamber’s role in promoting private sector development. The meeting was attended by ECCSA Deputy Secretary General Ms. Helen Reta and the Federation’s Vice Chairman, Mr. Li Lifei.
Members of the Chinese delegation, representing the Federation and various companies, expressed their interest in investing in Ethiopia, particularly in real estate development, manufacturing, energy supply, and other sectors. They highlighted Ethiopia’s potential as an attractive destination for business and investment.

