Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 19, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ከቻይና ይው (Yiwu) ከተማ ከተውጣጡ ኩባንያዎች ጋር ተወያዩ፡፡

  

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ከቻይና ይው (Yiwu) ከተማ ከተውጣጡ ኩባንያዎች ጋር ተወያዩ፡፡
ዋና ጸሐፊው ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በኢትዮጵያ ስለተካሄደው የኢኮኖሚ ሪፎርም፣  በኢንቨስትመንት ምቹ እድሎችና  ምክር ቤቱ በሚያከናውናቸው ተግባራት ዙሪያ ገልጸውላቸዋል፡፡
በኢትዮጵያ በተለይም ትኩረት በተሰጣቸው የግብርናና ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ በአይሲቲ፣ በማዕድንና በሌሎችም ዘርፎች በኢትዮጵያ መዋዕለንዋያቸውን እንዲያፈሱና ከኢትዮጵያ ኩባንያዎች ጋር በጋራ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል ዋና ጸሐፊው፡፡


ኩባንያዎቹ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች መስራት እንደሚፈልጉም በውይይታቸው አንስተዋል፡፡
በማዕከላዊ ዘጂያንግ ግዛት የሚገኘው የቻይናው ይው (Yiwu) በተለይም በጅምላ ንግድ ትልቅ ኢኮኖሚ የሚንቀሳቀስበት አካባቢ ነው፡፡
በውይይቱም የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎችና ሰላሳ የሚሆኑ የይው ከተማ ኩባንያዎች ተሳትፈዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia