Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 19, 2026 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ አካሄደ

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ አካሄደ
አዲስ አበባ፣  ሐምሌ11ቀን  2018 ዓ.ም  የጠቅላይ ሚኒስትሩ አረንጓዴ አሻራ (Green Legacy Initiative) ብሔራዊ ኢኒሼቲቭን በመደገፍ ተስፋን እንትከል በሚል  በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አስተባባሪት   በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ክፍለ ከተማ ሳህሊተ  ምህረት አካባቢ  የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ.  የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሣሁን ጎፌ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት አቶ ሰብስብ አባፊራ፣ የምክር ቤቱ የቦርድ አባላት፣ ማኔጅመንትና ሰራተኞች፣ከአባል ምክር ቤቶች  የኦሮምያ፣ የአዲስ አበባና  የሸገር  ከተማ አስተዳደር ንግድ ምክር ቤቶች የተውጣጡ ኃላፊዎችና ሰራተኞችም በመገኘት የአካባቢ ጥበቃና የአረንጓዴ ልማት ጥረቱን አጠናክረዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዶ/ር ካሣሁን ጎፌ ባስተላለፉት መልዕክት  የጠቅላይ ሚኒስትሩ አረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም እና ለቀጣይ ትውልድ አረንጓዴ ኢትዮጵያን ለመገንባት ያለውን ወሳኝ ፋይዳ በማብራራት፣ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ በቀጣይነት ሊጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።


በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ምክር ቤቱ በየዓመቱ የአባል ንግድ ምክር ቤቶችን በማስተባበር የንግዱ  ማህበረሰብ  የራሱን አረንጓዴ አሻራ እያሳረፈ መሆኑን ገልጸዋል። የንግዱ  ማህበረሰብ  ከኢኮኖሚያዊ ሚናው ባሻገር ማህበራዊ ሀላፊነቱን በተግባር እየተወጣ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም፣ የንግዱ ማህበረሰብ በአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት ውስጥ ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅሰው፣ በየደረጃው ያሉ የንግድ ምክር ቤቶች የንግዱን ማህበረሰብ በማስተባበር በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርና በሌሎች የማህበራዊ ሀላፊነት ተግባራት ድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ  የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከአባል ንግድ ምክር ቤቶቹ ጋር በመተባበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን በቀጣይ ዓመታትም የበለጠ በማጠናከር እንደሚቀጥል ተጠቁሟል ። ይህም የአካባቢ ጥበቃን ከማጠናከር ባሻገር የንግድ ማህበረሰቡ ለዘላቂ ልማትና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል።
ሐምሌ 11 ቀን 2018 የግሉ ዘርፍ አረንጓዴ አሻራ ተብሎ ሁሉም አባል ም/ቤቶች በየአካባቢያቸዉ በዛሬዉ ዕለት ችግኝ እየተከሉ መሆኑ ታዉቋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia