Oct 07, 2025 .
የገንዘብ ሚኒስቴር በጭማቂ አምራቾች ላይ የተጣለውን የዓመታት የኤክሳይዝ ታክስ ክፍያ ውሳኔ አገደ

የገንዘብ ሚኒስቴር በጭማቂ አምራቾች ላይ የተጣለውን የዓመታት የኤክሳይዝ ታክስ ክፍያ ውሳኔ አገደ
የገንዘብ ሚኒስቴር ፍራፍሬ ነክ መጠጥ አምራቾች ከስድስት ዓመት በፊት በወጣ ደንብ ምክንያት ያልተከፈለ የኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፍሉ የሚያስገድደውን የገቢዎች ባለስልጣን ውሳኔ አግዷል።
ይህ ውሳኔ የተሰጠው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የታሸገ መጠጥ የፍራፍሬ ጭማቂ ተብሎ እንዲታሰብ ቢያንስ 30 በመቶ የፍራፍሬ ይዘት ሊኖረው ይገባል የሚል ማብራሪያ ከሰጠ በኋላ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ይህንን መስፈርት አያሟሉም ያላቸውን አምራቾች የ4 ዓመት የኋላ ታክስ እንዲከፍሉ አስገድዶ ነበር።
የገንዘብ ሚኒስቴር ግን ውሳኔው የአገር ውስጥ አምራቾችን ሥራ እንዲዘጉ በማስገደድ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን እና ከውጭ ከሚገቡ ምርቶች ጋር ያላቸውን ተወዳዳሪነት እንደጎዳ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የቀረበለትን ቅሬታ ተከትሎ ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ግልጽ ባልሆነ የሕግ አጻጻፍ ምክንያት ከሸማቾች ያልተሰበሰበውን ዕዳ በአምራቾች ላይ መጫን ፍትሃዊ አይደለም በማለት ከዉሳኔ መድረሱን አስታውቋል።
#CapitalNews

