Jun 30, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ልዑክ ወደ ናይጄሪያ አበባ: ስጋ: ቡና እና ሰሊጥ ለመውሰድ ፍላጎት ካሳዩ የግሉ ዘርፍ ጋር ዉጤታማ ወይይት አካሂዷል።


ከናይጄሪያ የንግድ ማዕድን ኢንዱስትሪና ግብርና ም/ቤት ጋር የልምድ ልዉዉጥ ለማድረግና የሁለቱን አገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነትን ለማጠናከርና ማሳለጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር እንዲሁም የቢዝነስ ለቢዝነስ ግንኙነቶችን ለማመቻቸት ወደ ናይጄሪያ አቡጃ የተጓዘዉ የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ልዑክ ከኢትዮጵያ ወደ ናይጄሪያ አበባ ስጋ ቡና እና ሰሊጥ ለመውሰድ ፍላጎት ካሳዩ የናይጄሪያ የግሉ ዘርፍ ጋር ዉጤታማ ወይይት አካሂዷል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዓይናለም አባይነህ እና ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በናይጄሪያ ቆይታቸዉ ከናይጄሪያ የንግድ ማዕድን ኢንዱስትሪና ግብርና ም/ቤት እና ከናይጄሪያ የግሉ ዘርፍ ጋር የሁለቱን አገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነትን ለማጠናከር የተደረገዉን ዉይይት ወደ ተጨባጭ ተግባር መቀየር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በዛሬዉ ዕለት በናይጄሪያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ለገሰ ገረመዉ ጋር ፍሬያማ ዉይይት አድርገዋል።

