Read more

Jul 01, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከተለያዩ ኩባንያዎች ተወካዮች ጋር በንግድ፣ ፋይናንስና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከተለያዩ ኩባንያዎች ተወካዮች ጋር በንግድ፣ ፋይናንስና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

ምክር ቤቱ Financial Barriers to Trade in Ethiopia: credit, collateral, Interest rate, and Foreign Exchange Volatility  በሚል ርዕሥ በወጡ አዋጆችና አሠራሮች ዙሪያ ባንኮችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ነው የዴስክ ሪቪው (Desk Review) ውይይት ያካሄደው።

በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌ ምክር ቤቱ ከተሠጡት ኃላፊነቶች አንዱና ዋነኛው የምርምርና አድቮኬሲ መሆኑን በማንሣት በዚህም በፋይንሥ ዘርፉ እና የንግድ እንቅስቃሴው ምቹ ሁኔታ ዙሪያ የምርምርና አድቮኬሲ ሥራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።

የምክር ቤቱ የሪሰርች እና አድቮኬሲ ቡድን መሪ አቶ ታከለ አየለ በተለይም ከወጡ አዋጆችና አሠራሮች ጋር በተያያዘ ምክር ቤቱ ያካሄደውን ዳሰሳ አቅርበዋል።

በዚህም ከፋይናንስ አቅርቦት፣ ማሥያዣ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ፣ ብድር አሠጣጥ፣ ማስያዣ (collateral)፣ የወለድ ምጣኔ፣ በብድርና ቁጠባ ተቋማት እንዲሁም በወጭ እና ገቢ ንግድ ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮችን እንዲሁም ያሉትን መልካም አጋጣሚዎችና ምቹ ሁኔታዎች በውይይቱ ተዳሰዋል።

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ተክቶ መጠቀም፣ ከብድር አቅርቦት፣ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የተሻለ የፋይናንሥ አቅርቦት እንዲኖር፣ በፋይናንስ ጥያቄ በኩል አሥፈላጊ መረጃዎችን ማሟላትና ከባንኮች አሠራር ጋር የተጣጣመ መሆን እንዳለበትና በመሣሠሉ ሀሣቦች ዙሪያ ሠፊ ውይይት ተደርጓል።

 

በምክር ቤቱም በተነሱና የንግድ ሥራውን የተሣለጠ ማድረግ የሚያስችሉ የጥናትና የአድቮኬሲ ሥራዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚከናወኑ ተጠቁሟል።

በውይይቱም፣ ባንኮች፣ ላኪዎች፣ የሴቶች ማኀበራት፣ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ተወካዮች እንዲሁም የሌሎች ኩባንያዎች ተወካዮች ተገኝተዋል።

Manni Maree Daldalaafi Waldaalee Seekeroota Itoophiyaa halla dhiyeessii Faayinaansii, Tajaajila.Liqiifi Sharafa biyya alaa walliin wal qabatee rakkoowwan hawaasa daldalaa quunnamanirratti bakka bu’oota dhaabbilee daldalaa, omishtootaafi al-ergitootaa, akkasumas dhaabbilee Faayinaansii waliin marii taasiseera.

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia