Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Feb 26, 2025 .

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የንግድ ኤግዚቢሽን ሳምንት በይፋ ተከፍተ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የንግድ ኤግዚቢሽን ሳምንት በይፋ ተከፍተ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ የተከፈተው ይህ ኤግዚቢሽን “የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ሲሆን ከዛሬ ነሃሴ 19 ቀን 2016 ዓም ጀምሮ እስከ ነሃሴ 23 ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፤  የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እንዲሁም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ስብስብ አባፊራ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች፣የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡ ከኤግዚቢሽኑ ጎን ለጎን የፓናል ውይይቶችን ጨምሮ የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚካሄዱ ሲሆን ገዥና ሻጭን ማገናኘት እንዲሁም በዘርፉ ግንዛቤን ለማሳደግ የሚረዱ መርሃ ግብሮች እንደሚኖሩም ተገልጿል ፡፡

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜም ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች በቋሚነት ለእይታ የሚቀርቡበት ቦታም ተከፍቷል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia