Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Feb 26, 2025 .

በአኩሪ አተር ምግብ ልየታ ፤ አዘገጃጀት እና አጠቃቀም ላይ ያደረገ የሶስት ቀናት ስልጠና በሀዋሳ እየተካሄደ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ም/ቤት የተዘጋጀውና ትኩረቱን በአኩሪ አተር ምግብ ልየታ ፤  አዘገጃጀት እና አጠቃቀም ላይ ያደረገ የሶስት ቀናት ስልጠና በሀዋሳ እየተካሄደ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀኃፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ትኩረቱን በአኩሪ አተር ምግብ ዝግጅት ላይ ያደረገው የስልጠና መድረክ ዋንኛ መነሻም ምክር ቤታችን  የግሉን ዘርፍ አቅም በመገንባት ረገድ የሚጠበቅበትን ለመወጣት ነው፡፡

ስልጠናው በዋንኛነት  በሶስት ክልሎች ማለትም  በኦሮሚያ፤ አማራ እና ሲዳማ የሚሰጥ ሲሆን   በአኩሪአተር ምርት ልማት ላይ እየተሳተፉ ያሉ  የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም የንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ፤ኮፕሬቲቭሰ፤ አምራቾች ፤ የአምራቾች ማኅበራት እና የምግብ አቀነባባሪዋች  በቂ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ እና የሚያገኙት እውቀትና ክዕሎትም በተግባር ላይ በማዋል አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ለውጥ እንዲያመጡ ማስቻል ሌላኛው ዓላማው ነው፡፡

አክለውም፤ ለዘርፉ ተዋንያን ተገቢውን ስልጠና በመስጠት  የሚታየውን የክህሎት ክፍተት መሙላት፤  ክህሎትን በማሳደግ ኢንዱስትሪው እንዲስፋፋ፣ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር እና ተወዳዳሪነት እንዲጎለብት ማስቻል ከስልጠናው የሚጠበቅ ውጤት ነው ፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia