4ኛዉ ሃገራዊ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የጋራ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
ኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉ 4ኛዉ ሃገራዊ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የጋራ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀዉ 4ኛዉ ሃገራዊ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የጋራ የምክክር መድረክ( PPD) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ሚኒስትሮች፣ የክልል ፕሬዚዳንቶ፣ ጥሪ የተደረገላቸዉ አምባሳደሮችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ነው በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ አዳራሽ ነሐሴ 23 ቀን 2016 ዓ.ም የተካሄደ ው፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) መንግስት ተወዳዳሪ የንግድ ስርዓትን ለመገንባት፣ የገቢና የወጪ ንግዱን ለማሳለጥ በርካታ የፓሊሲና የህግ ማሻሻያዎችን ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ ምክክር መደረጉ በንግድ ሥርዓት ውስጥ የሚያጋጥሙን ክፍተቶች በጋራ ተወያይቶ ለመፍታት ከማገዙም ባሻገር ፤ የንግድ ስርዓቱን ለማዘመን፣ በዘርፉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት፣ የልማት አጋርና አብሮ የመስራት ባህልን ለማዳበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል ሲሉ ገልጸዋል።
በመድረኩ በበጀት ዓመቱ የተሻለ የንግድ ስራ አፈጻጸም ላሳዩ የንግድ ድርጅቶች የእውቅና ሰርቴፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡ቡና፣አበባ፣ የቅባት እህልና የጥራጥሬ ምርቶችን በመግዛት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሀገራትም እውቅና ተሰጥቷል።