Feb 26, 2025 .
አዲሱ ዓመት የጤና፤ የሰላም እና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ለመላው ህዝባችን እና የንግዱ ማኅበረሰብ አዲሱ ዓመት የጤና፤ የሰላም እና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ ይመኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለግሉ ዘርፍ እድገት አመቺ የሚሆን ንቁና አስቀድሞ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የምክር ቤት አሰራር ሥርዓት ሰፍኖ ማየት፣ የሚለው ራዕዩን ዕውን ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአዲስ የአሰራር እና አስተሳሰብ ወደተግባር መግባቱን እያበሰርን፤ በዚህም ስትራቴጂካዊ ግቦቻችንን እንደምናሳካና የግሉ ዘርፍ ዘመኑን በሚዋጅ ደረጃ ለማድረስ እንደምንሰራ ቃል እንገባለን ፡፡
በድጋሚ አዲሱ ዓመት የጤና፤ የሰላም እና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ

