Feb 26, 2025 .
የክልልና የከተማ የንግድና የዘር ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ለተውጣጡ ዋና ጸሃፊዎች የዲጂታል ስልጠና
የኢትዮጵያ የንግድና የዘርፍ ማህራት ምክር ቤት ከGIZ-SEQUA በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከተለያዩ የክልልና የከተማ የንግድና የዘር ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ለተውጣጡ ዋና ጸሃፊዎች የዲጂታል ስልጠና እየሰጠ ነው።
የስልጠናውን መጀመር አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የምክር ቤቱ ዋና ጸኀፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ የስልጠናውን ፋይዳ ገልጸው ፤ በተለይም የዲጂታል ኦላይን አገልግሎት አጠቃቀም ግንዛቤን ማሳደግእንደ ሀገር የግሉን ዘርፍ መረጃ ለማደራጀት፣ የመረጃ አያያዝን ለማዘመን ያግዛል፣ ይህም ወቅቱ የሚጠይቀውን የዲጅታል ቴክኖሎጅ በመጠቀምና በመተግበር ስራ ለመስራት አስተዋጾው ጉልህ ነው ብለዋል።
አያይዘውም ይህ የዋና ጸኃፊዎች ስልጠና ምክር ቤቶችን የሚመሩ ኃላፊዎች የሚሰጥ በመሆኑ የግሉን ዘርፍ ለመደገፍና ለማዘመን እንዲሁም ዓለማቀፍ ተወዳዳሪነት ያለው ምክር ቤት ለመገንባት የምናደርገው ጥረት ለማሳካት ትልቅ አበርክቶ ያለው ስልጠና መሆኑን ጠቅሰው ምክር ቤቱ ከተሰጡት ተልዕኮ አንዱ የአባል ምክር ቤቶችን አቅም ለማጎላበትና ለማሳደግ የተለያዩ ስልጠናዎ እየተሰጡ ነው ፣የምርምርና አድቮኬሲ የንግድና የኢንቨስትመንት ስራዎችንም ለማሳለጥ እየሰራን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

