Feb 26, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዓይናለም አባይነህ ከማይንማር አምባሳደር ጋር ተወያዩ፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዓይናለም አባይነህ ከማይንማር አምባሳደር ጋር ተወያዩ፡፡
በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ግብጽ፣ ሞሮኮ የማይንማር አምባሳደር ኪያው ቲን ሼን እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ባሉት የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚደንቱ ዶክተር ዓይናለም በኢትዮጵያ በኩል ባሉት የንግድ እና ኢንቨስትመን እድሎች ዙሪያ ለአምባሳደሩ አብራርተውላቸዋል፡፡
በማይንማር በኩልም ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት የማጠናከር ፍላጎት መኖሩን ገልጸው በአዲስ አበባም ኤምባሲዋን እንደምትከፍት ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያም በሩቅ ምስራቅ ሀገራት በኩል ለሚኖራት የንግድ ግንኙነት የማይንማርን ወደቦችን ለመጠቀም የምትችልባቸው እድሎች ስለመኖራቸው የተጠቆመ ሲሆን በሀገራቱ መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብርን ለማሳደግም የሁለቱ ሀገራት የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች ተቀራርበው መስራት እንደሚገባቸው ተጠቅሷል፡፡

