Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

May 29, 2025 .

የሸገር የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ጋር በልምድ ልውውጥ መድረክ ዙሪያ ተወያዩ፡፡

የሸገር የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 23 ቀን 2017  የሚያካሂደውን  የልምድ ልውውጥ መድረክ በማስመልከት ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ጋር ተወያየ።

የሸገር የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት መጋቢ ስርዓት ቄሲስ ታዬ ለታ በጋራ የውይይት  መድረኩ ላይ እንደገለጹት ፤ ምንም እንኳን መርሐ ግብሩ የሚዘጋጀው በሸገር የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ቢሆንም ለፕሮግራሙ ስኬት የኢትዮጵየ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ትብብርና እገዛ ወሳኝ ነው።


የኢትዮጵያ ን/ዘ/መ/ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) በበኩላቸው የሸገር ን/ዘ/ማ/ም/ቤት ከተመሰረት አጭር ጊዜ ቢሆንም ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያከናወናቸው ስራዎች ይበል የሚያሰኙና ሊበረታቱ የሚገቡ መሆናቸውን አንስተው  ም/ቤቱ  ላከናወናቸው ተግባራት አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

የልምድ ልውውጥ መርሐ ግብሩን ለማሳካት አስፈለጊውን ተቋማዊ እገዛ ከማድረግ ባሻገር ለሁለንተናዊ ስኬቱ  የኢ/ን/ዘ/ማ/ም/ቤት ምንጊዜም እገዛው እንደማይለያቸውም አረጋግጠዋል።

   

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia