Jun 03, 2025 .
የንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ከንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ደኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ (ዶ/ር ) ጋር ተወያዩ፡፡

ከኢፌዴሪ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ደኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ (ዶ/ር ) ጋር የክልል እና የከተማ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች አደረጃጀትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙርያ ዉይይት መደረጉን የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር ገለጹ ::
በውይይቱም ሚኒስትር ደኤታው መንግስት የግሉን ዘርፍ ለማጠናከር እንዲቻል ብዙ ስራዎችን ከንግድ ምክር ቤቶች ጋር እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም በየደረጃው ያሉት ምክር ቤቶች እንዲጠናከሩና የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ሚኒስቴር መ/ቤታቸው የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል::


