Jun 05, 2025 .
ዶክተር ዓይናለም አባይነህ በኢትዮጵያ ከታይላንድ አምባሳደር ሞራኮት ጃንማቱኮርን ጋር ተወያዩ፡፡


የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ዓይናለም አባይነህ በኢትዮጵያ ከታይላንድ አምባሳደር ሞራኮት ጃንማቱኮርን ጋር ተወያዩ፡፡
ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል ስለሚኖረው የኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በቢዝነስ ግንኙነቶች ዙሪያ ነው የተወያዩት፡፡
ዶክተር ዓይናለም አባይነህ ምክር ቤቱ በሚሰራቸው ስራዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ስላሉ መልካም እድችና የሁለቱን ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንት እድሎች ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ለአምባሳደሯ አብራርተውላቸዋል፡፡
አምባሳደር ሞራኮት በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች መካከል ያለውን የቢዝነስ የጋራ ተጠቃሚነት ማስፋት እንደሚገባ፤ የሀገራቱ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶችም ተቀራርበው መስራት እንደሚገባቸውና ለዚህም በትኩረት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡


በውይይቱም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌ፣ በኬንያ የታይላንድ ኤምባሲ 2ኛ ጸሐፊ ተራዌ ጉራድቶፕን ጨምሮ ሌሎች ተወካዮችም ተገኝተዋል፡፡

