Jun 25, 2025 .
የአትዮጵያ የንግድና ኢንቨሥትመንት ፎረም ኩባንያዎች ከሌሎች አቻዎቻቸው ጋር በጋራ ለመሥራት እድል የሚፈጥር መሆኑን መጋቢ ሥርዓት ታየ ለታ ተናገሩ።



በሥካይላይት ሆቴል በተካሄደው የኢትዮጵያ የንግድና ኢንቨሥትመንት ፎረም ላይ የተገኙት መጋቢ ሥርዓት ታየ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከውጭ ጉዳይ ሚኒሥቴር እና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር መሠል የልምምድ ልውውጥ በማዘጋጀት እና በጋራ ለመሥራት እየተጋ መሆኑን አንሥተዋል።
የኢትዮጵያ እና የቻይና ኩባንያዎችም በተለያዩ የንግድና ኢንቨሥትመንት አማራጮች የሚያደርጓቸው የትብብር ሥራዎች ለጋራ ተጠቃሚነት የላቀ ሚና እንዳላቸውም በማጠቃለያ ንግግራቸው ላይ ጠቁመዋል።ከኢትዮጵያና ከቻይና ተውጣጡ ኩባንያዎችም በጋራ በሚሰሩባቸው ዘርፎች ዙሪያ የቢዝነስ ለቢዝነስ ውይይት አካሂደዋል፡፡




