Jul 08, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ::


የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ::
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ዋና ፀኃፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ(ተባባሪ ፕሮፌሰር) እና የማኔጅመንት አባላት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱም የምክር ቤቱ ዋና ፀኃፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ(ተባባሪ ፕሮፌሰር) የምክር ቤቱን ታሪካዊ ዳራ ፣የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች እንዲሁም ምክር ቤቱ እየተገበራቸው ያሉ የንግድና ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን፣የጥናትና ምርምር እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስራዎች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት መሆኑን ሰፊ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ስራ አስኪያጅ መልዕክተ ሳህሉ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አድንቀው አብሮ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል፡፡ በውይይቱ ማጠቃለያም ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግየኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጋር በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ:: የስራ ኃላፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ተጠናቋል፡፡




