Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Jul 14, 2025 .

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደር ዶክተር መሀመድ ካሊድ ጋር ተወያይተዋል።

 

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር በኢትዮጵያ የአልጄሪያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አምባሳደር ከሆኑት ዶክተር መሀመድ ካሊድ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ሁለቱ ኃላፊዎች በሁለቱ ሀገራት መካከል ስላለው የንግድና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ተስፋዎች ተወያይተዋል። ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ የረጅም ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ቢኖራቸውም ኢኮኖሚያዊ እና የንግድ ትስስራቸው ጥሩ እንዳልሆነ አውስተው የሁለቱም ሀገራት የንግድ ምክር ቤቶች የሀገራቱን የንግድና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ተባብሮ መስራት አለባቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሪዘዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር በሁለቱም ሀገራት የንግድ ግንኙነት ውስጥ ያሉትን ምቹ ሁኔታዎችና ተስፋ ገልፀው፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከአልጄሪያ የንግድ ምክር ቤት ጋር ለመተባበር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የአልጄሪያ አምባሳደር እና በአፍሪካ ህብረት እና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቋሚ ተወካይ ዶ/ር ሞሃመድ ካሊድ አልጄሪያ ለቡና እና ሌሎች የኢትዮጵያ ምርቶች መዳረሻነት ተመራጭ መሆኗን እንዲሁም በሁለቱም ሀገራት የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ሁለቱ ወገኖች በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ ትርኢቶች እና በሌሎች በርካታ ኢንዱስትሪዎች ለሚደረጉ የቢዝነስ ጥግንኙነቶች ተግባራዊነት መተባበር እዳለባቸውም አምባሳደሩ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ፣ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) እና የአልጄሪያ ተልዕኮ ዲፕሎማቲክ አታሼ ጋህድር አብደራኦፍ በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል።

Sebsib Abafira Abajobir, president of the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), discussed with Dr. Mohamed Khaled, ambassador of the People’s Democratic Republic of Algeria to Ethiopia, at his office.

The two parties discussed about the prospects for business and economic relations between the two nations. Ethiopia and Algeria have long-standing diplomatic and people-to-people relationships, though their economic and trade relations are not well developed. As a result, both countries’ chambers of commerce must collaborate to strengthen the countries’ trade and economic ties, as discussed.

Sebsib Abafira Abajobir, president of the ECCSA, explained the prospects present in both nations’ business relationships and stated that the ECCSA is committed to collaborating with the Algerian Chamber of Commerce. Dr. Mohamed Khaled, ambassador of Algeria to Ethiopia and permanent representative to the AU and UNECA, elaborated on Algeria’s potential for trading, including coffee and other Ethiopian products, as well as investment opportunities in both countries.

Both sides highlighted the commitment that must be made for practical efforts in trade, investment, trade fairs, and other business endeavors across many industries. Dr. Kenenisa Lemie (Associate professor), the secretary general of the Ethiopia Chamber of Commerce and Sectoral Associations, and the diplomatic attaché of Algeria’s mission in Ethiopia,Ghedir Abderaouf, also attended the discussion.

 

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia