Jul 22, 2025 .
በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራዉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ልዑክ የዘመናዊ አዉቶሞቢሎችና ቀላል የጭነት ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ጎብኝቷል።

በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የተመራዉ የም/ቤቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ልዑክ ከሱማሌ ክልል የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የቦርድ አባላት ጋር በመሆን በSAHID MI Engineering የሚሰራ የከባድ መኪና አካል ማምረቻና መገጣጠሚያ እና SWUEYS MOTERS COMPANY የተሰኘ የዘመናዊ አዉቶሞቢሎችና ቀላል የጭነት ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ወቅት አምራች ኢንዱስትሪዉ በሱማሌ ክልል በአበረታች ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና በመንግስት በኩል ተገቢዉ ድጋፍ ሊደረግላቸዉ እንደሚገባ አቶ ሰብስብ አሳስበዋል።
የSAHID MI Engineering ባለቤት አቶ አብዱራህማን ሳሂድ በድርጅታቸዉ መጎብኘት የተሰማቸዉን ደስታ ገልፀዉ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ክልል ወርዶ የስራ ጉብኝት አድርጎ የግሉን ዘርፍ ማነቃቃትና ለማበረታታት መጀመሩ ታሪካዊና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ ተግባር ነዉ ብለዋል።



