Jul 23, 2025 .
ችግኝ መትከል ለሰው ብለን የምናደርገው ቀላል ነገርም አይደለም! ከምንገምተው በላይ ትልቅ አንድምታ ያለው ሀገራዊ ጉዳይ ነው!!




ፖለቲካ አይደለም!
ለሆነ አካል የምንውለው ውለታ አይደለም! ለሰው ብለን የምናደርገው ቀላል ነገርም አይደለም! ከምንገምተው በላይ ትልቅ አንድምታ ያለው ሀገራዊ ጉዳይ ነው!! ለነገው ትውልድ ቅሪት የማስቀመጥ፣ ነገ የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልድ የመገንባት፣ ዛሬን ተሻግረን ነገን ማሰብ ነው!!
ተስፋን በትውልድ ቅብብሎሽ መሃል ማኖር ነው!! ሀገርን የመውደድ ምልክት ነው!! ትላንት አባቶቻችን ያቆዩልንን የተከበረች ሀገር እኛም በጊዜያችን በጣም የተሻለች ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ ትልቅ አሻራ ነው!! ሀገር የወል እውነታችን ናት።
የሁላችንም ቤት ናት። በዘር፣ በቀለም፣ በፆታ፣ በሀይማኖት፣ በትውልድ አከባቢ ሳንገደብ ለኢትዮጵያችን የምናኖረው ትልቅ ታሪክ ነው። ይህ ለሀገር የምንከፍለው ዋጋ ነው!
ይህ ግን የማያልፍ ቋሚ ቅርስ ነው!! ይህ ኢትዮጵያችንን በአለም ከፍ የማረግ ተግባር ነው!! ይህ በፈተና መሃል የምናሳካው ጣፋጭ ድል ነው!!
ይህ ስምን ከመቃብር በላይ የምናረግበት የታሪክ መወደሻ መንገድ ነው!! ይህ እኛ አስቀምጠን አልፈን ነገ ትውልድ ስማችንን እየዘከረ የሚኖርበት ነው! ይህ ለኢትዮጰያ ነው!!!!!
ችግኝ እንተክላለን!!!!



