Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Aug 25, 2025 .

የኢትዮጵያን ይግዙ” 3ኛው ሲዲ-ቻምበር 2018 ዓዲስ አመት ዋዜማ የንግድ ሳምንት ኤግዚብሽን እና ባዛር በሀዋሳ ከተማ ተከፈተ።

“የኢትዮጵያን ይግዙ” 3ኛው ሲዲ-ቻምበር 2018 ዓዲስ አመት ዋዜማ የንግድ ሳምንት ኤግዚብሽን እና ባዛር በሀዋሳ ከተማ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በተገኙበት በይፋ ተከፈተ።

የሲዳማ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ከሲዳማ ክልል የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እና ከቢኒያም ፕሮሞሽን ሰርቪስ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ “የኢትዮጵያን ይግዙ” 3ኛው ሲዲ-ቻምበር ባዛር እና ኤግዚቢሽን በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አማካኝነት ተመርቆ ተከፍቷል።

የኢትዮጵያን ይግዙ” የተሰኘ ልዩ የንግድ ሳምንት ዛሬ በይፋ የተከፈተ ሲሆን ኤግዚብሽን እና ባዛሩ ከነሐሴ 17/2017 እስከ ጳጉሜ 5/2017 ዓ. ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን በአገር ውስጥ የተመረቱ ምርቶችን በማስተዋወቅ፣ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት በማሳደግ እና ለሸማቾች ጥራት ያላቸውን የአገር ውስጥ ምርቶች ተደራሽ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው በኤግዚብዤን እና ባዛሩ ምረቃ ወቅት ተገልጿል።

ኤግዚብሽን እና ባዛሩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ ዋና ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መርቀው የከፈቱ ሲሆን ጉብኝትም አድርገው በታላቅ ድምቀት አስጀምረውታል ሲል የሲዳማ ክልል የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት በላከልን መረጃ አሳዉቋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia