The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) and GIZ-ETC have signed a project starting agreement

The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) and GIZ-ETC have signed a project starting agreement focused on strengthening the Technical and Vocational Educational Training (TVET) system and enhancing private sector involvement.
The agreement aims to ensure that businesses benefit from a skilled and qualified workforce while fostering stronger relationships between the private sector and TVET stakeholders. It also seeks to align with the broader strategic objectives established in the TVET ecosystem.
At the signing ceremony, Dr. Kenenisa Lemie, Secretary General of ECCSA, and Muhammad Ali Khan, Regional Finance Manager of GIZ-ETC, formalized the agreement.
To improve the private sector’s engagement, ECCSA has already established a specialized TVET unit at its headquarters. The project is set to be implemented over a two-year period.

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) እና የጂ አይ ዜድ ቀጣናዊ የፋይናንስ ማናጀር ሙሀመድ አሊ ካሃን በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እና በግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
በስምምነቱ ወቅት እንደተገለጸውም የፕሮጀክቱ እውን መሆን የሰለጠነና ብቃት ያለው የሰው ኃብት በማፍራት የቢዝነስ ዘርፉን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችል ነው፡፡
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና (TVET) ልዩ ትኩረት በመስጠት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዩኒት ያቋቋመ ሲሆን በፕሮጀክቱ ትግበራ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
ፕሮጀክቱም ለ2 ዓመታት ተግባራዊ እንደሚደረግ በስምምነቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡

