Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 08, 2025 .

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ መክፈቻ አፍሪካ የአየር ንብረት ተጠቂ ብቻ ሳትሆን የመፍትሄውም አኅጉር መሆኗን በአፅንኦት ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ መክፈቻ መርሃግብር አፍሪካ የአየር ንብረት ተጠቂ ብቻ ሳትሆን የመፍትሄውም አኅጉር መሆኗን አፅንኦት ሰጥተው በመግለፅ ከፍተዋል።

እንደአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ ሥራ፣ ለአየር ንብረት ጥበቃ የተመቸ ግብርና እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በማውሳትም የኢትዮጵያን ሥራዎች በምሳሌነት በማንሳት አውስተዋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ከአየር ንብረት ርዳታ ወደ አየር ንብረት ኢንቨስትመንት ለውጥ ሊደረግ እንደሚገባ በመግለጽ Climate Innovation Compact የተሠኘ በ2030 1000 አፍሪካ መር መፍትሔዎች የሚገኙበትን ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል።

አፍሪካ በታዳሽ ኃይል፣ በምግብ ዋስትና እና የሥነ ምኅዳር ጥበቃ  የመምራት አቅሟንም በማጽናት አንስተዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ እኤአ በ2027 የCOP32 ጉባኤን ለማስተናገድ ያላትን ጥያቄም አቅርበዋል። ይኽም ሀገራችንን እና አኅጉራችንን በአየርንብረት ጥበቃ ተግባር የመሪነት ሚና የሚያጎናፅፍ ይሆናል።


This morning Prime Minister Abiy Ahmed opened the Second African Climate Summit in Addis Ababa, emphasizing Africa’s role as a continent of climate solutions rather than a victim of the crisis.

He highlighted Ethiopia’s initiatives, including the Green Legacy tree-planting campaign, climate-smart agriculture, and the Grand Ethiopian Renaissance Dam, as examples of sustainable development.

The Prime Minister called for a shift from climate aid to climate investment, proposed an African Climate Innovation Compact to deliver 1,000 African-led solutions by 2030, and underscored Africa’s potential to lead in renewable energy, food security, and ecosystem restoration.

He also announced Ethiopia’s candidacy to host COP32 in 2027, positioning the nation and the continent as global leaders in climate action.

#PMOEthiopia

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia