Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 12, 2025 .

ኢትዮጵያ እና ኢስዋቲኒ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ለስኳር የሚሆን የሸንኮራ አገዳ ልማት ላይ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰዋል፡- አቶ አዲሱ አረጋ

ኢትዮጵያ እና ኢስዋቲኒ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ለስኳር የሚሆን የሸንኮራ አገዳ ልማት ላይ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መድረሳቸውን የግብርና ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ ገልጸዋል፡፡

የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ራስል ሚሶ ዲላሚኒ ከግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ ጋር በመሆን፣ በጅማ ዞን የቡና ልማት ሥራዎችን እንዲሁም በጅማ ከተማ የኮሪደር ልማትን እና የአባ ጅፋር ቤተ-መንግስትን ጎብኝተዋል።

‎በጉብኝቱ የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ራስል ሚሶ ዲላሚኒ በጅማ ዞን ከሚገኙ ለዓለም ገበያ ቡናን ከሚያቀርብ አምራች አርሶአደሮች ጋር መወያየታቸው ተገልጿል።

በዚህም ከኢትዮጵያ የቡና ልማት እና ከሌሎች የግብርና ልማት ሥራዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልምድ መውሰዳቸው ተጠቅሷል፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ሁለቱ ሀገራት በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በሸንኮራ አገዳ ልማት በጋራ ለመስራት ከመግባባት ደርሰዋል። ebc

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia