Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Sep 23, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና CIPE EHIOPIA የተሰኘ አለም አቀፍ የግል ዘርፍ ኢንተርፕራይዝ ማዕከል  የግሉ ዘርፍ በአገሪቱ የኢኮኖሚና የሰላም ግንባታ ውስጥ ሊኖረው በሚገባ ሚና ዙርያ በጋራ ለመስራት ተወያዩ፡፡

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና CIPE EHIOPIA (Center for International Private Enterprise)  የተሰኘ አለም አቀፍ የግል ዘርፍ ኢንተርፕራይዝ ማዕከል  የግሉ ዘርፍ በአገሪቱ የኢኮኖሚና የሰላም ግንባታ ውስጥ ሊኖረው በሚገባ ሚና ዙርያ በጋራ ለመስራት ተወያዩ፡፡

በኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ በአገር ኢኮኖሚ እና  ሰላም ግንባታ ውስጥ ተገቢውን ሚና እንዲጫወት ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የግሉ ዘርፍ ድምፅ የሆነው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና  በአለም አቀፍ ደረጃ የዲሞክራሲ ስርአት እንዲጎለብትና ገበያ ተኮር ማሻሻያዎች እንዲደረጉና የግሉ ዘርፍ ሚና እንዲጎላ ለማድረግ የሚሰራው በኢትዮጵያ አለም አቀፍ የግል ዘርፍ ኢንተርፕራይዝ (CIPE) አብሮ ለመስራት ምክክር አድርገዋል፡፡

 

የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) እና የCIPE ETHIOPIA ዳይሬክተር አቶ ኃይለመለኮት አስፋው የአገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ መጎልበት እንዳለበት በውይይታቸው ያነሱ ሲሆን ለዚህ ዋነኛ መሰረት በሆነው የሰላም ጉዳይ ላይ በጋራ እንደሚሰሩና አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም አቶ ኃይለመለኮት አሳውቀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያ ፕሮግራምን እውን ለማድረግ የሚረዳውን ዲጂታል ኢኮኖሚ ተግባራዊ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የግሉን ዘርፍ አቅም ለማጎልበትም አብሮ ለመስራት ሁለቱ ተቋማት ተስማምተዋል፡፡

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia