በመዲናዋ ከ3 ሺህ በላይ ባለሐብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ ገብተዋል::

በመዲናዋ ከ3 ሺህ በላይ ባለሐብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ ገብተዋል::
በአዲስ አበባ በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ባለሐብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገልጿል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አይሻ መሀመድ እንደገለጹት፤ በ2017 በጀት ዓመት 8 .5 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ከ3 ሺህ 200 በላይ ባለሐብቶች ፍቃድ ወስደው ወደስራ ገብተዋል፡፡
ኮሚሽኑ ለባለሐብቶቹ የተለያዩ ማበረታቻዎችን እያቀረበ እንደሚገኝም ጠቁመው፤ ከማበረታዎቹ መካከል እንደ ዘርፎቹ የገቢ ግብር እፎይታ ከ3 እስከ 5 ዓመት እንዲሁም የማምረቻ ቦታ እና ማሽነሪ ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በተያዘው በጀት ዓመትም ከ3 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ኢንቬስተሮች ፈቃድ ይሰጣል እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡
ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል እንዲያስመዘገቡ እንዲሁም ከ7 ሺህ 500 በላይ ለሚሆነ ዜጎችም የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታውቀዋል።
በዘርፉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማዘመን የኢንቨስትመንት ፍሰቱን ለማሳደግ፣ አዲስ አበባ ያላትን እምቅ ሀብት ማስተዋወቅ፣ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ማሳለጥ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በቅንጅት የመፍታት ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።
ኢንቨስትመንቱን ለማሳደግ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነሯ፤ ባለፈው በጀት ዓመት የማምረቻው ዘርፍ አፈፃፀም ከፍተኛ እንደነበር አስታውሰዋል።
ምንጭ – EBC

