Sep 24, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች ለተሠማሩ ሴቶች ሥልጠና እየሠጠ ነው።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች ለተሠማሩ ሴቶች ሥልጠና እየሠጠ ነው።
ሥልጠናውም በማርኬቲንግ እና በቢዝነስ ሊደርሺፕ ላይ ያተኮረ ነው።
በሥልጠናው ማሥጀመሪያ ላይ የምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሠር) የኢኮኖሚው ዋና አንቀሣቃሽ የሆኑት ሴቶች አቅማቸው እንዲጎለብትና ውጤታማ ቢዝነስ መሥራት እንዲችሉ ምክር ቤቱ ትኩረት ሠጥቶ እየሠራ ሥለመሆኑ ገልጸዋል።


ሰልጣኞችም ሥልጠናውን በአግባቡ በመከታተል የሚያገኙትን እውቀት ተግባራዊ በማድረግ ዘመናዊና ጊዜው የዋጀ ቢዝነስ መምራት እንደሚገባቸውም አሥገንዝበዋል።
ሰልጣኞችም በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ በቡና፣ አልባሣት፣ በባልትና እንዲሁም በሌሎች የቢዝነስ ዘርፎች የተሠማሩ ናቸው።

