የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከካናዳ ኤምባሲ ሲንየር ትሬድ ኮሚሽነር ጋር ዘላቂ በሆነ ተቋማዊ ግንኙነትና ትብብር ዙሪያ ምክክር አደረገ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከካናዳ ኤምባሲ ሲንየር ትሬድ ኮሚሽነር ጋር ዘላቂ በሆነ ተቋማዊ ግንኙነትና ትብብር ዙሪያ ምክክር አደረገ።
በውይይቱ የክልሉ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቦጋለ ቢታኔ ከአማካሪዎቻቸው ጋር በመሆን ከካናዳ ኤምባሲ ልኡካን በተለይም ሲንየር ትሬድ ኮሚሽነር ማርክ- አንድሪ ሳቫጅ እና ከንግድ ኮሚሽነሯ ሰሎሜ ወንድሙ ከተመራ ልኡክ ጋር ክልሉ ስላለው ብዝሀ ሀብትና ፀጋ እንዲሁም ጠንካራ መሰረት ያለው የትብብር ማእቀፍ ለመገንባት የሚያስችል ውይይት በተለይም
– በአግሮ ፕሮሰሲንግ (በቡና፣በቅመማቅመም፣በሆርቲካልቸር…)
– በዘላቂ ቱሪዝምና ኢኮ ቱሪዝም
– እንዲሁም ታዳሽ ኃይልና ማይኒንግ ዘርፍ ላይ በላቀ የጋራ ተጠቃሚነት ለመስራት የሚያስችል ጥልቅ ውይይትና ተግባቦት ላይ የደረሰ ፍሬያማ ምክክር ተደርጓል።

አቶ ቦጋለ ቢታኔ የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ይህ ትብብር ወደላቀ ውጤት እንዲሸጋገር በቁርጠኝነት ለመስራት የልኡካን ቡድኑ ያሳየውን ቁርጠኝነት በማድነቅ የዚህ መሰረት በክልሉ ከፍተኛ የውጪ ኢንቬስትሜንት ፍሰት እንዲኖር በማስቻል፣የላቀ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር በማድረግ ብሎም የሚተገበርና የሚታይ እሴት ለንግድ ማህበረሰባችን በመጨመር የክልላችንን ብዝሀ ሀብት አሟጠን በመጠቀም ተጠቃሚነታችንና ስኬታማነታችንን ለማረጋገጥ በምናደርገው ጉልህ ተግባር ላይ የሚያስቀምጠው አሻራ የላቀ መሆኑን በመግለፅ ልኡካን ቡድኑን አመስግነዋል።
ልኡካኑም ከከተማው ከንቲባ ክቡር ዶ/ር መስፍን መንዛ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ ወ/ሮ ልሳነወርቅ ጋር እንዲሁም ከጋሞ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዋኖ ዋሎሌና ማኔጅሜንታቸው ጋር የተሳካ የትብብር ማእቀፍ ውይይት አድርገዋል።
ይህ ምክክርና የጋራ ትብብር እንዲሳካ የላቀ አስተዋፅኦ ያበረከቱትን በተለይም ኢንጂነር ስለእናት ደሪባን በምክር ቤቱና በክልሉ የንግድ ማህበረሰብ ስም ለማመስገን እንወዳለን።
ምንጭ- (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት)

