Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 07, 2025 .

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በተለያዩ የቢዝነስ መሥኮች ሥልጠና ለሚሠጡ አሠልጣኞች ሥልጠና እየሠጠ ነው።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በተለያዩ የቢዝነስ መሥኮች ሥልጠና ለሚሠጡ አሠልጣኞች ሥልጠና እየሠጠ ነው።

ከSNV – LIWAY ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የአሰልጣኞች ሥልጠና የቢዝነስ ተቋማትን አቅም ለመገንባት ያለመ ነው።

አሠልጣኞቹም በዲጂታል ማርኬቲንግ፣ በማሥተዋወቅ እና ብራንዲንግ እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ ማርኬቲንግ እና በሌሎችም መሥኮች ሥልጠናዎችን የሚሠጡ ናቸው።

የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌ በሥልጠናው ማስጀመሪያ ላይ እንደገለጹት የአባላትንና የቢዝነስ ተቋማትን አቅም እንዲያድግ እንዲሁም የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ሥምምነት ትግበራ፣ የአለም ንግድ ድርጅት አባልነትን ታሣቢ ያደረገ ቢዝነስ እንዲኖር በማለም የተዘጋጀ ሲሆን ቀጣይነት ያለው ነው።

ሥልጠናውን በአጋርነት ያዝጋጀው SNV የተሠኘው ዓለም አቀፍ ተቋምም በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ፕሮጀክቶች ላይ እየሠራ ያለ ተቋም ነው።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከሚሠጣቸው አገልግሎቶች አንዱ ለንግዱ ማኀበረሰብ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሥጠት መሆኑ ይታወቃል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia