Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 09, 2025 .

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ በተመለከተ የፓናል ውይይት ተካሄደ።

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ በተመለከተ የፓናል ውይይት ተካሄደ።

የፓናል ውይይቱ በተለይም Uገሪቱ ከምትተገብረው የኢኮኖሚ ሪፎርም አንፃርና በመንግስትና በግሉ ዘርፍ መካከል ባለው ግንኙነት ዙሪያ ያተኮረ ነው።
በውይይቱ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ዋና ጸሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ ተወካይ፣ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆብርና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የንግዱ ማኀበረሠብ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሀብረቢ በአወያይነት በተሠየሙበት የፓናል ውይይት የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፉ ማህበራት ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር)ን ጨምሮ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ተወካዮች በፓናሊስትነት ተሣትፈዋል።

ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሠር) ምክር ቤቱ ከትግበራውና የግሉ ዘርፍ ሚና ጋር በተያያዘ በስምምንቱ ዙሪያ የላቀ ግንዛቤ እንዲኖር ለማድረግ የስልጠናና የአቅም ግንባታ ስራዎች በስፋት ሲሰራ እንደነበርና ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል : :

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia