Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Oct 22, 2025 .

የተሻሻለው የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

▶️ የተሻሻለው የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡

▶️ የፖሊሲው ክፍል  4.7.2  የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማጠናከር  በሚለው ንዑስ-ርዕስ ስር:

▶️ የግሉ ዘርፍ የግብርና ቴክኖሎጂ፣ ግብዓትና አገልግሎትን በማቅረብ፣ በቀጥታ ምርት ማምረት፣ ግብይትና  እሴት ጭመራ አገልግሎቶች ላይ በመሳተፍ ለግብርና ምርትና ምርታማነት እድገት ያለው አስተዋጽዖ
ከፍተኛ ነው ሲል የሚያስቀምጥ ሲሆን። በተጨማሪም፦

▶️ የግሉ ዘርፍ በግብርና ልማትና ግብይት ውስጥ ያለው ተሳትፎና ውጤታማነት ከፍተኛ ፋይዳ  ቢኖረውም ከአገልግሎትና ሌሎች ዘርፎች ጋር ሲነፃፃር የግብርና ልማት ከፍተኛ ልፋት የሚጠይቅ፣  ለከፍተኛ ሥጋት (risk) የተጋለጠ በመሆኑ፣ የትርፍ ህዳጉ ዝቅተኛ ስለሆነ የግሉን ዘርፍ በግብርና  ልማት ውስጥ በሚፈለገው ደረጃ ለማሳተፍ እና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል የዘርፉን ልዩ ባህሪያት
ያገናዘበ የአሰራር ሥርዓት አልተዘረጋም።

▶️ በተጨማሪም በማደግ ላይ ያሉ አነስተኛ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮችን በመደገፍና በማበረታታት ወደ ኢንቨስትመንት ለማሻገር የሚያስችል በቂ ትኩረትና የአሰራር ሥርዓት አልተዘረጋም። ሲል ይቀጥላል ….

❇️❇️❇️❇️❇️
ለመሆኑ የተሻሻለው የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ ምን ይዟል? ፖሊሲውን በዝርዝር ለመረዳት ለሚሹ ከላይ አያይዘነዋል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia