Oct 27, 2025 .
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በብራንዲንግ እና አድቨርታይዝመንት ዘርፍ ለተለያዩ የቢዝነሥ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሥልጠና እየሠጠ ነው።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት በብራንዲንግ እና አድቨርታይዝመንት ዘርፍ ለተለያዩ የቢዝነሥ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሥልጠና እየሠጠ ነው።
ምክር ቤቱ ከሚሠራቸው ዋና ዋና ሥራዎች መካከል የአቅም ግንባታ እና ሥልጠና አንዱ ነው።
ሥልጠናው የሚሠጠው ምክር ቤቱ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እንዲሁም ከSNV- LIWAY ፕሮጀክት ባገኘው ድጋፍ ነው።
የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ጸደቀ ድጋፌ በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ቢዝነሶች በሀገር ውሥጥም ሆነ በአፍሪካና በሌላው ዓለም ዘንድ ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ ምክር ቤቱ ተከታታይ ሥልጠናዎችን እየሠጠ መሆኑን ገልፀዋል።



በቢዝነስ አመራር አካዳሚ በኩል በዲጂታል ቴክኖሎጅ አጠቃቀም፣ ምርትና አገልግሎትን በማሥተዋወቅ እና በምርትና አገልግሎት ብራንዲግ እንዲሁም በሌሎችም ዘርፎች ቀጣይነት ያላቸው ሥልጠናዎች እንደሚሠጡም ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ ከሣምንት በፊት ተከታታይ የአሠልጣኞች ሥልጠና ሲሰጥ መቆየቱ ይታወቃል።

