Oct 27, 2025 .
ኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የስራ አመራር አባላት የምክር ቤቱን የመጀመርያዉን ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የስራ አመራር አባላት የምክር ቤቱን የመጀመርያዉን ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂደዋል።
የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የምክር ቤቱ የስራ አመራር አበላት በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈፃፀማቸዉን የመገምገም ባህል እንዳልነበራቸዉና ከባለፈዉ በጀት ዓመት ጀምሮ ግን የዕቅድ አፈፃፀም በየሩብ ዓመቱ እየገመገሙ በአፈፃፀም ላይ የታዩ ጉድለቶችን ነቅሶ በማዉጣት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን እያስቀመጡ መሄድ ስለተጀመረ ስራዎችን በታቀዱት መሰረት ለመከወን መቻሉን አስረድተዋል።


