ልዩ መብት የተፈቀደላቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ፕሮግራምን ለመወሰን የሚያስችል መመሪያ ቁጥር 1081/2017

ልዩ መብት ?
ከአለም የጉምሩኮች ድርጅት የንግድ ማሳለጥ እና ደህንነት ማዕቀፍ (SAFE Framework of Standards) ስታንዳርድ ጋር የተጣጣመ ልዩ መብት የተፈቀደላቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ፕሮግራም በመቅረጽ ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ፤
በዓለም አቀፍ ንግድ እና በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ተሳትፎ ያለው ሰው በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት እየተመዘነ ልዩ መብት የተፈቀደላቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ፕሮግራም የሚታቀፍበትን እና የሚተዳደርበትን አሰራር ለመወሰን በማስፈለጉ፤
ከፍተኛ ስጋት ያላቸውን ጭነቶች የመለየት አቅምን በማሻሻል እና በጉምሩክ አስተዳደሮች መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ደህንነቱ የተጠበቀ አለማቀፍ የሸቀጦች ፍሰትን የሚያበረታታ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፣
ለሕግ ተገዥ የሆኑትን በማበረታታት ለንግድ፣ ለአምራች ኢንዱስትሪው እና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ቀለል ያለ፣ ፍትሐዊ፤ ፈጣን እና ተገማች የጉምሩክ አገልግሎት በመስጠት የኢኮኖሚ ልማትን መደገፍ በማስፈለጉ፤
በንግዱ ማህበረሰብ እና በመንግስት ተቋማት መካከል አጋርነት እና መተማመንን በማጠናከር የአገራችን ኢኮኖሚ እንዲጎለብት የሚያደርግ ሥርዓት ተግባራዊ ማድረግ በማስፈለጉ፤
የገቢዎች ሚኒስቴር በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 (እንደተሻሻለ) አንቀጽ 180 (2)
በተሰጠው ስልጣን መሰረት
ልዩ መብት የተፈቀደላቸው የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ፕሮግራምን ለመወሰን የሚያስችል መመሪያ ቁጥር 1081/2017 አውጥቷል፡፡ መመሪያው ምን ይዟል?
Read the full PDF Document.
1081_2017_ልዩ_መብት_የተፈቀደላቸው_የኢኮኖሚ_አንቀሳቃሾች_ፕሮግራምን_ለመወሰን_የወጣ_መመሪያ_ቁጥር

