Nov 05, 2025 .
ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የአለም ንግድ ድርጅት የአባልነት የሁለትዮሽ የገበያ ድርድር በማጠናቀቅ ተፈራረመች፦ ክቡር ዶክተር ካሣሁን ጎፌ።


ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የአለም ንግድ ድርጅት የአባልነት የሁለትዮሽ የገበያ ድርድር በማጠናቀቅ ተፈራረመች፦ ክቡር ዶክተር ካሣሁን ጎፌ።
ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር የአለም ንግድ ድርጅት የአባልነት የሁለትዮሽ የገበያ ድርድር መጠናቀቋን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢትዮጵያ የአለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር አካል የሆነው የሁለትዮሽ የገበያ ድርድር ከቱርክዬ እና አርጀንቲና ጋር ባለፉት ሳምንታት መፈረሙን ያስታወሱት ክቡር ሚኒስትር ዛሬ ሶስተኛውን የገበያ ድርድር ስምምነት ስዊዘርላንድ- ጄኔቫ በሚገኘው ኤምባሲያችን አማካይነት ተፈራርመናል ብለዋል።
ሚኒስትሩ ከዚህ ጋር አያይዘው ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራትም ጋር ተመሳሳይ ድርድሮችን በማፋጠን ላይ ትገኛለች ብለዋል። ን/ቀ/ት/ሚ

