Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 05, 2025 .

ለኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የቦርድ አባላትና ለምክር ቤቱ የኮሙኒኬሽንና ፕሮቶኮል ባለሙያዎች የቢዝነስ እና አለምአቀፍ ፕሮቶኮል ሥልጠና ተሠጠ።

ለኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና ለምክር ቤቱ የኮሙኒኬሽንና የፕሮቶኮል ሰራተኞችና አመራሮች ከኢፌዲሪ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር  የቢዝነስ እና አለምአቀፍ ፕሮቶኮል ስልጠና ተሰጠ፡፡

ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒሥቴር ጋር በመተባበር የተሠጠው ሥልጠና ምክር ቤቱ የቢዝነስ ዲፕሎማሲ ስራዎችን የሚሠራ በመሆኑ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተመላክቷል።

የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አቶ ሰብስብ አባፊራ አባጆብር በሥልጠናው ላይ እንደገለጹት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት በሚሠሩ የቢዝነስ ዲፕሎማሢ ሥራዎች የፕሮቶኮል አሠራሮችን መከተል ውጤታማ ሥራዎችን ለመሥራት አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል።

ሥልጠናውን የሠጡት በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመንግስት ፕሮቶኮል፣ ሴርሞኒ እና ኮንፍረንስ ዳይሬክተር አቶ እሸቱ ለገሰ ናቸው።

ከእንግዳ አቀባበል ጀምሮ በግንኙነት አግባቦች ተግባራዊ መደረግ ባለባቸውና ሊተገበሩ የሚገባቸው ጉዳዮችም ተዳሠዋል።

ለሀገራዊ የንግድና ኢንቨስትመንት መሥፋፋት፣ ለቢዝነስ ግንኙነቶች ማደግ፣ ለፓለቲካዊ፣ ባህላዊና ማህበራዊ ግንኙነት መዳበርና ሀገራዊ ገጽታን ለመገንባት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት የፕሮቶኮል መርሆችን መተግበር በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑም በሥልጠናው ላይ ተጠቁሟል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia