Mon - Fri: 8:30 - 05:30 PM
info@ethiopianchamber.com

Read more

Nov 06, 2025 .

ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ከራሽያ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሥራ አስፈፃሚ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ማክሲም ኦሬሽኪን እና የራሽያ አቻቸው ውይይት አካሂደዋል።

የኢፌድሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በዛሬው ዕለት የራሽያ ልኡካን ቡድንን መርተው ከመጡት ከራሽያ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሥራ አስፈፃሚ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ማክሲም ኦሬሽኪን እና የራሽያ አቻቸው የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ሬሼንኮቭ ጋር በሁለቱ ሃገራት ንግድና ኢኮኖሚያዊ ትስስሮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አካሂደዋል።

ሁለቱ ሃገራት ዘመናትን የተሻገረ ጠንካራ ሁለንተናዊ ትብብር ያላቸው ሲሆን በመካከላችን ያለውን የሁለትዮሽ የንግድ ትስስርን ይበልጥ ለማጠናከርና በባለብዙ ወገን ማዕቀፍም በትብብር ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

 

በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት ካለን የህዝብ ብዛት፣ ኢኮኖሚና ታሪካዊ ግኙነት አንጻር ሲታይ ገና ብዙ መስራት እንዳለብን የሚያሳይ መሆኑን የጋራ መግባባት ላይ መደረሱንም አውስተዋል። ወደፊትም የኢትዮጵያን ምርቶች በጥራትና በብዛት ወደ ራሽያ ገበያ ለመላክ ያለንን ዕምቅ አቅም አስረድተዋል።

በራሽያ በኩልም ኩባንዎቻቸው በኢ-ንግድና አውቶሞቢል ዘርፍ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነትን በታለመው ጊዜ ለማሳካት የራሽያ ፌዴሬሽን የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ድርድርን በቀጣይ ሳምንት ሞስኮ በሚካሄደው የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ ለመፈረም ቃል ገብተዋል። በባለብዙ ወገን ድርድርም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።ን/ቀ/ት/ሚ

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations

Contact Info

Mon - Fri : 8:00 AM - 05:00 PM
Sat : 8:00 - 06:00 PM
+251 115 514 005
info@ethiopianchamber.com
+251-115-517699
517

Office Address

Mexico Square, Addis Ababa, Ethiopia