የጫት ላኪነት የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ የወሰዱ ላኪዎች የንግድ ስራ ፈቃድ ማውጣት፣ ማደስ ወይም ማሻሻል የሚችሉት የብቃት ማረጋገጫውን ከወሰዱበት ቀን አንስቶ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ብቻ ነው፡፡

የጫት ወጪ ንግድ የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ
ማስታወቂያ….ለላኪዎች
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር የ2018 በጀት ዓመት የጫት ወጪ ንግድ የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ፣ አዲስ የንግድ ስራ ፈቃድ እና ነባር የንግድ ስራ ፈቃድ ዕድሳት መስጠት የጀመረ በመሆኑ በ2017 በጀት ዓመት የጫት ወጪ ንግድ የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ ወስደው የንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ ወይም አዲስ ፈቃድ ያወጡ በ2018 በጀት ዓመት የጫት ወጪ ንግድ የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ መውሰድ ሳያስፈልጋቸው የንግድ ፈቃዳቸውን ማደስ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
በ2017 በጀት ዓመት የጫት ወጪ ንግድ የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ ያልወሰዱ ወይም አዲስ ላኪዎች ከህዳር 01/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 30/2018 እንዲሁም የጫት ወጪ ንግድ ሥራ ፈቃድ እስከ ታህሳስ 30/2018 የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በዚሁ መሠረት ላኪዎች አዲስ አበባ ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ሴንቸሪ ሞል አጠገብ በሚገኘው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የወጪ ንግድ ግብይት የስራ ክፍል በግንባር በመቅረብ አዲስ የቅድመ ፈቃድ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና የንግድ ስራ ፈቃድ እንዲያወጡ፣ነባር የንግድ ፈቃዳቸውን እንዲያሳድሱ ወይም እንዲያሻሽሉ እያሳሰብን ከታህሳስ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለነባርም ሆነ አዲስ የጫት ላኪነት ንግድ ስራ ፈቃድ ጠያቂዎች የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የመስጠት አገልግሎት የሚቆም መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- የጫት ላኪነት የቅድመ ፈቃድ ብቃት ማረጋገጫ የወሰዱ ላኪዎች የንግድ ስራ ፈቃድ ማውጣት፣ ማደስ ወይም ማሻሻል የሚችሉት የብቃት ማረጋገጫውን ከወሰዱበት ቀን አንስቶ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ብቻ ነው፡፡
(የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር)

