Nov 16, 2025 .
ክቡር አምባሳደር ዳባ ደበሌ ከTully’s Coffee Japan Co, Ltd. ፕሬዚዳንት ጋር ውይይት አደረጉ::

ክቡር አምባሳደር ዳባ ደበሌ ከTully’s Coffee Japan Co, Ltd. ፕሬዚዳንት ጋር ውይይት አደረጉ፣
መቀመጫውን ጃፓን በማድረግ የተለያዩ አለማት ላይ ቡና በመሸጥ ተዋቂ ከሆነው Tully’s Coffee ጋር ውይይት የተደገ ሲሆን በእለቱ ክቡር አምባሳደር ዳባ ደበሌ የኩባንያው ፕሬዚዳንት ከሆነቱ Shuji Uchiyama ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ላይ ክቡር አምባሳደር የቡና ምርትን ለመጨመረ በአገራችን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በተመለከተ ሰፊ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት መንግስት ባከናወነው ከፍተኛ ስራዎች ለኢንቨስትመንት እና ንግድ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸዋል።
Shuji Uchiyama በበኩላቸው ለተደረገላቸው ማብራሪያ ምስጋና በማቅረብ የኢትዮጵያ ቡና በደንበኞቻቸው ዘንድ ከፍተኛ ደረጃ ተፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል። በመጨረሻም በተደረገው ውይይት በቀጣይ ከኤምባሲው ጋር የኢትዮጵያ ቡና ለማስተዋወቅ በቅርበት እንደሚሰሩ መግባባት ላይ ተደርሷል።
ምንጭ:በቶኪዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

