ሁለተኛው የኢትዮ ሳዑዲ የጋራ ንግድ ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ ራዲሰን ብሉ ሆቴል ተካሂዷል፡፡

ሁለተኛው የኢትዮ ሳዑዲ የጋራ ንግድ ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ ራዲሰን ብሉ ሆቴል ተካሂዷል፡፡
የጋራ ምክር ቤቱ ስብሰባ መጀመርያ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ንግድ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰብስብ አባፍራ አባጆቢር በኢትዮ-ሳዑዲ የጋራ ንግድ ምክር ቤት ማዕቀፍ መሰባሰብ ለሁለቱ አገሮች ትልቅ ዕድል መሆኑን በመግለፅ የጋራ ምክር ቤቱ በሁለቱ አገሮች መካከል ጠንካራ የውይይት፣ የትብብርና አጋርነት መድረክ ሆኖ የሚቀጥል ነው ብለዋል፡፡
ይህ በኢትዮጵያ የተካሄደው ሁለተኛ የጋራ የንግድ ምክር ቤቱ ስበሰባም የቀጣይ ትብብራችን አካል ነው ያሉት አቶ ሰብስብ በሁለቱ አገራት የንግድ ባህበረሰቦች መካከል ያለውን ጥልቅ ግንኙነት ከሚያንፀባርቁ በርካታ መድረኮች አንዱም ነው ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባልና የኢትዮ-ሳዑዲ ያጋራ ንግድ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብሳቢ መጋቢ ስርዓት ታዬ ለታ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ይህ የጋራ ምክር ቤት መቋቋሙ በኢትዮጵያና በሳዑዲ አረቢያ መካከል ቀጣይነት ያለው ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት ለምናደርገው ጥረት እንደ አንድ ጠንካራ እርምጃ የሚወሰድ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት የገለፁት መጋቢ ታዬ የትዮጵያና ያዑዲ ኢንተርፕራይዞች ትርጉም ያለው ውይይት እንዲያደርጉ፣ የገበያ መረጃ እንዲለዋወጡና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያመጡ ስራዎችን እንዲያዳብሩ እንደሚያስችላቸውም አስረድተዋል፡፡
በሳዑዲ አረቢያ የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ የሆኑት አብዱላህ አልአጂሚ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት መካከል የጋራ ምክር ቤት መቋቋሙ የመንግስቶቻችንን የጋራ ራዕይ ወደ ተግባራዊ የኢኮኖሚ ውጤቶች በመተርጎም ስራን የሚፈጥር፣ ዕድገትን የሚያነቃቃና የንግድ ፍሰቶችን የሚያጎለብት ነው ብለዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድርም የተሳተፉ ሲሆን አሁን ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ካደረገው የኢኮኖሞ ሪፎርሞች ጋር ተያይዞ በርካታ የሳዑዲ ባለሀብቶችን ሊያሳትፉ የሚችሉ ዘርፎች መኖራቸውን በኢትዮጵያ በኩል የተገለፀላቸው ሲሆን ከሳዑዲ የመጡ የጋራ ምክር ቤቱ አባላትም የሳዑዲ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማረግ ፍላጎት እንዳለቸው አስረድተዋል፡፡የኢትዮ- ሳዑዲ የቢዝነስ ፎረም በነገው ዕለት በማሪዮት ሆቴል ይካሄዳል፡፡

